Monday, June 11, 2012
Friday, April 1, 2011
My country
የኢትዮጵያ ሕዝብ ከረጂም ጊዜ ጀምሮ
አመታት ለነፃነትና ለዲሞክራሲያዊ ስርዓት መስፈን ባደረጉት መራራ ትግል በቁርጥ ቀን ዜጎች ደም ሃገራዊ ህልዉናዋ ለዘመናት
ተጠብቆና ተከብሮ የኖረች አገር ብትሆንም እንኳን ከራሷ በፈለቁ ለሃገርና ለወገን ስቃይና እንግልት ደንታ ቢስ በሌላቸዉ ጨቋኞችና
አስተዳደራዊ ስርአትን ባልተላበሱ መሪዎችና አስተዳዳሪዎች ዛሬም እየደማች እና እየቆሰለች ትገኛለች። ዜጎች በሃገራቸዉ ማህበራዊ
ኑሮአቸዉን በሰላማ መንገድ የመምራት፤ የዜግነት መብታቸዉን የመጠበቅ፣የማክበር፣የመምርጥ፣በነጻ የመንቀሳቀስ መብቶቻቸዉ በግፈኛ
ገዢዎች መዳፍ ስር ታፍኖ ኑሮአቸዉን በስቃይ እና በፍርሃት ተሸብበዉ የኢትዮጵያዊነት ስሜታቸዉ ተገፎ በመኖርና በሞት ጣር ዉስጥ
ተዘፍቀዋል። የኢህአዴግ መንግስት በዉጭ ያለዉን ዲፕሎማሲያዊና ግንኙነቱንና በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎችና በምዕራባዉያኑ ያለዉን
ጥቅማ ጥቅሞች ለማስከበር ደፋ ቀና አያለ የዲሞክራሲንና የሰብአዊ መብቶችን እንደሚአከብርና የዜጎችን መብትና ነጻ እንቅስቃሴ
እንደሚአከብር ራሱ ባዘጋጃቸዉ ሚዲያዎች ሁለተኛ ፕሮፖጋንዳዉንና የአስመሳይነት ባሕሪዉን ቢያንጸባርቅም እንኳን በድብቅ እና
በገሃድ የሚያራምደዉን የአፈና ፣የእስራትና የግድያ ወንጀሎቹ ለአደባባይ በገሃድ ፍንትዉ ብለዉ ወጥተዋል። በኢትዮጵያ ዉስጥ
ያለዉን የሰብአዊ መብት አካሄድ በምን ሁኔታ ላይ እንዳለ እና የሕአዴግ መንግስት በህዝብ በፕሬስ -አፈና፣ እስራት ግድያ፣በጅምላ
ጭፍጨፋ፣ በተለያዩ ጊዜዎች ባካሄዳቸዉ ጦርነቶች ዉስጥ የፈጸማቸዉ ልዩ ልዩ የጦርነት ወንጀለኞች እና የሰብአዊ መብቶችን በመጣስ
ላይ ያለ አምባገነን መንግስት መሆኑን፡ ዋና ጽ/ቤቱ አሜሪካን አገር የሆነዉ “ፍሪዶም ሃዉስ” በመባል የሚታወቀዉ ዓለም ዓቀፍ
የእንባ ጠባቂ ተቋም ዓመታዊ ሪፖርት ላይ ገልጿል:፡ ስለዲሞክራሲና ስለ ዜጎች መብት የሚለፈልፍልን የኢሕአዴግ/የህወሓትና
በእነርሱ ስር የታቀፉ እና የጭቆና ኣላማቸዉን በየክልሉ ተግባራዊ ለማድረግ የፈለፈሏቸዉ ፖለቲካዊ ስፋን በሰጣቸዉ ፓርቲዎቹ
ኢስብአዊ አመራር ተግባራዊ ያደርጋል። በሌላ በኩል “ሂዩማን ራይትስ ዎች” የተባለ የሰብአዊ መብት ጠበቃ ድርጅት ባወጣዉ
የ2008 ኣመታዊ አጠቃላይ ሪፖርቱ ላይ እንደሚያመለክተዉ በተቃዋሚዎችና ትችት ሰንዛሪዎች ላይ ጠንከር ያለ እርምጃ እየተወሰደ
ነዉ።የኢትዮጵያ የጦር ሃይሎች የተለያዩ የጦርነት ወንጀሎችን መፈጸሙን የቀጠለ ሲሆን በተለይም በሱማሌ ክልል በኦጋዴን እና
እንዲሁም በሶማሊያ በሰፊዉ ታይቷል” ይላል። የኢሕአዴግ መንግስት ለመጪዉ የምርጫ ሂደት ዝግጅት ይመስላል። አገር ዉስጥ
ሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚዎችን ባገኘዉ አጋጣሚና አቅጣጫ እንቅስቃሴአቸዉን በማዳከም እና በሃሰት በመወንጀል ለእስራት በመዳረግ በአገሪቱ
ዉስጥ ያለዉን የፖለቲካ እና የህዝብ እንቅስቃሴ ከሕግ ዉጭ በሆነ አፈና እና ወታደራዊ አፈና በተላበሰ እንቅስቃሴ ይገኛል።
የሕአዴግ መሪዎች ካለፈዉ ምርጫ የሕዝቡን ስሜትና የዲሞክራሲ ጥማቱን እና ብሎም ለኢሕአዴግና ተከታዮቹ ያለዉን ጥላቻ የተገነዘቡ
ይመስለኛል።
Thursday, March 31, 2011
Our heros
Aberash Berta, who has been imprisoned by Woyane since 1993, for the Milton Friedman Prize for
Advancing Liberty. A prize of $500,000 is made every other year to an individual
like Aberash Berta who has made great contribution to advance human rights.
Their website is: www.cato.org/special/friedman/about.htmlJust
log in to their website and click “2010 Friedman Prize Nominations” on the
right-hand side or click the following link: www.cato.org/special/friedman/prize/friedmanform.html
Aberash Berta: Disappeared since 1993As a young woman she joined the Ethiopian
people’s Revolutionary Party (EPRP established in 1972) struggling against the
totalitarian Soviet backed regime of Mengistu Haile Mariam. She served no regime
in any capacity. She fought for democracy in Addis Ababa and later on in rural
areas with EPRP guerrillas and was wounded and was blinded in one eye. Aberash
was captured by the incumbent Ethiopian regime of Mr. Meles Zenawi in Addis
Ababa in mid 1993 a few days after EPRP leadership member Gebre Igziabher (Gaym)
was martyred. She has been disappeared since along with Lemma Makonen and
Tesfaye Kebede. For a while there was news that she was being held in Holeta,
outside of Addis Ababa, and that she was not in good health. But later there was
absolutely no news of her condition and that of her comrades. Inexplicably,
local and international human rights bodies have chosen to remain silent on her
case. Let us raise our voices calling for the release of Aberash Berta, a
political prisoner for the last 16 years, by recognizing the price she paid for
the respect of democratic rights in Ethiopia.
ተጋድሎ ሓርነት ህዝቢ ትግራይን ከመሰረቱት መሃል ሦስቱ ማለትም ዶ/ር አረጋዊ በርሀ (“በሪሁን”) አቶ ግደይ ዘርአጽዬን (“ፋንታሁን”) ደ/ር ዓለምሰገድ መንገሻ (ሃይሉ) እንዲሁም የሕዝባዊ ሓርነት ትግራይ የእስር ቤቶች እና የድርጅቱ ስለላዉ ክፍል ከፍተኛ ባለስልጣን የነበረዉ አቶ ብስራት አማረ፤ በርሀ ሓዱሽ፤መኮንን ዘለለዉ (ፋኑስ) እና ሌሎቹ ሆነዉ በየካቲት ወር 1987 ዓ.ም (በፈረንጅ ፌብሩዋሪ 1995) TAND Tigrean Alliance for National Democracy በመባል የሚመሩት የፖለቲካ ድርጅት፣ ሰሞኑን “የሗሊት ጉዞ አገራችንን ይበታትናል” በሚል ርዕስ ለጀነራል ሃይሌ መለስ የትግራይ ሕዝብ ወደ ትግሉ አልቀላቀልም አለ፤ ዝምታዉ እስከመቸ ነዉ? በማለት የተቹት ጽሁፍ የተሰጠ የድርጅቱ መግለጫ ሳነብብ፣ ድርጅቱ እቃወመዋለሁ የሚለዉንን ህወሓትን “እኛ የወያነ ስርአት ተቃዋሚዎች ” ‘በዘር/በጎሳ ያነጣጠሩ የግድያ የእንግልት እና የእስራት ድርጊቶች የምንላቸዉን ህወሓት የፈጸማቸዉ የጎሳ ጥላቻ መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች “ታንድ” ሲያብራራ “ህወሓት/ኢሕአዴግ ሰዉን የሚገድለዉና የሚያንገላታዉ ሥልጣኑ ላይ ሊያደርሰዉ ከሚችለዉ አደጋ አንጻር (ለአምባገነኖቹ አገዛዝ የማያመቹ በመሆናቸዉ ካልሆነ) እንጂ በዘሩ ነዉ ብለን አናምንም፣፣ በዘር ቢሆን ኖሮማ ከላይ የጠቀስናቸዉና ያልዘረዘርናቸዉ የትግራይ ልጆች በ(ህወሓት) ባልተገደሉ ነበር፣፣” በማለት በአረጋዊ፣ በግዳይ፣ በስብሓት እና በመለስ ዜናዊ የሚመራዉ የጥንቱም ሆነ የዛሬዉ “ወያነ ትግራይ” *አምባገነን ድርጅት* እንጂ *ጎሰኞች አይደለም!* ሲል “ምን ታመጡ!” በማለት ብዙዎቻችን በታንድ ላይ ያልነበረን ዕዉቀት የታንድ ማንነት ገሃድ ወጥቶ እንዲገለጽለጽልን መግለጫቸዉ ረድቶናል፣፣ ከዚህ ተያይዞ ሁለት ሌሎች የምተችባቸዉ ነገሮች አሉ። ልተችበት የምፈልገዉ ነጥብ “የትግራይ ሕዝብ ዝም ብሏል” ወደ ትግል አልገባ ብሎ በጣም አድፍጧል እና ለምን?” ብሎ ለጠየቀ ሁሉ “ጸረ ትግራይ ነዉ” እያሉ የሚለጥፉበትን ስም ነዉ። በዚህኛዉ ልጀምር፦ አዎ የትግራይ ሕዝብ ወደ ትግሉ አልተቀላቀለም፤ አድፍጧል ብሎ ያለዉ ሌላዉ የተቃዋሚ ክፍል ኢትዬጵያዊዉ ብቻ ሳይሆን ከእራሱ ከታንድ መሪዎች (የታንደ የሚዲያዉ ክፍል ሓላፊ) አቶ መኮንን ዘለለዉ በነሓሴ ባለፈዉ ወር ያረጋገጠዉ ነዉና ለምን ድነዉ ሌላዉ ሲለዉ ታንድ የሞቆጣዉ? አቶ መኮንን ዘለለዉ ከአዲስ ድምጽ ራዲዬ አዘጋጅ ከአቶ አበበ በለዉ ጋር ቃለ መጠይቅ ሲያደርግ ይህንን አረጋግጦታል። ልጥቀስ፤ ጥያቄ፦ ብዙ ሰዎች የትግራይ ሕዝብ ወደ ትግሉ አልተቀላቀለም፤ እያሉ ብዙ ሰዎች ይተቻሉ፤-ለምንድነዉ ወያኔን በስማችን መነገድ አቁም፤ በማለት በይፋ የማይቃወሙት?ሲሉ ብዙ ሰዎች ይተቻሉ እና እዉነት የትግራይ ሕዝብ ለምን ድምጹን በይፋ አያሰማም? ተብሎ ለቀረበዉ ጥያቄ ሲመልስ፤ አቶ መኮንን ዘለለዉ እንዲህ ብሎ ነበር “ (የትግራይ ሕዝብ) 90 ወይም መቶ በመቶ (የወያኔ) ተቃዋሚ ነዉ፤ ሚስቱ የከዳችዉ ሰዉ ተሎ ለመታገል ዝግጁ የሚሆን አይመስለኝም። የትግራይ ሕዝብ ባሳደጋቸዉ፤በልጆቹ የተከዳ ሕዝብ ነዉ። አንድ ሰዉ -የሚያምናት ሚስቱ በሚስቱ የተከዳ ሌላ ሚስት ለማግባት የሚሮጥ አይመስለኝም። ቆም ብሎ ማሰብ ያስፈልገዋል። ልጆቼ ብሎ ወደ ትግሉ የላከ ልጆቹ የካዱት ሕዝብ ነዉ። እና አሁን በቀጥታ ወደ ትግሉ ለመግባት የሚችል አይመስለኝም። እና ቆም ብሎ በማሰብ ላይ ነዉ። አርቆ የሚያስብ እዉነተኛ የሚታመን የትግል ድርጅት እስካሁን አልተገኘም። እከሌ አለ የምትልም አይመስለኝም። .......አሁን -የትግራይ ሕዝብ በጠቅላላ አሁን ኢትዬጵያዊ ዕምነት ያለዉ የትግራይ ሕዘብ እየጠፋ ነዉ….።” ሲል በግልጽ አቶ መኮንን ዘለለዉ የፍትሒ ራዲዬ አዘጋጅ በማያሻማ ቃል አስቀምጦታል ።የቃለመጠይቁ ቅጅ/አዉድዬዉ አሁንም በአዲስ ድምጽ የህዋ ሰሌዳ በመግባት ማዳመጥ ይቻላል። አቶ መኮንን “በጠቅላላ አሁን ኢትዬጵያዊ እምነት ያለዉ የትግራይ ህዘብ እየጠፋ ነዉ” ሲል “ምን ማለቱ” እንደሆነ አዘጋጁ ለምን እንዲያብራራለት በዝምታ እንዳለፈዉ ግራ ገብቶኛል። “ለመታገል ዝግጁ የሆነ አይመስለኝም። ቆም ብሎ በማሰብ ላይ ነዉ…” የሚሉት ሐረጎች ምንን ያመላክታሉ?18ዓመት ቆም ብሎ በዝምታ እያሰበ ነዉ ብሎናል። ዛሬም የሚታመን ኢትዬጵያዊ ድርጅት ካጣ “ታማኙና ተቆርቋሪዉ የትግራዋይ ታንድ ድርጅት” እንዴት አላምንም አለዉ? ወይስ ታንድም እንደሌሎቹ ኢትዬጵያዊ ድርጅቶች የትግራይ ሕዝብ አላምንህም በሎታል?ታንድ ከተመሰረተ ዓመታት አስቆጥሯል ለምን እሱን እንኳ አላመነዉም? የተቀሩትተቃዋሚ ኢትዬጵያዊ ድርጅቶች መኮንን ዘለለዉ ዉን ተመርኮዞ “ዝምታ በዛ፡ ቆም ብሎ ማሰቡ ረዘመ፤” ብሎ ለሚል ተቺ እንዴት “ጸረ ትግራይ ሕዝብ ያስብለዋል? ይህ ከላይ የተጠቀሱት የድርጅቱ ሁለቱ ኮምጣጣ አቋሞች ለሕሊናየ አስቸጋሪ ግብግብ ሆኖ አግንቼዋለሁ፣፣ ሌላዉ 2ኛዉ ነጥብ፤-ታንድ ባሰራጨዉ ጽሑፍ በገጽ 8ላይ ““ህወሓት/ኢሕአዴግ ሰዉን የሚገድለዉና የሚያንገላታዉ ሥልጣኑ ላይ ሊያደርሰዉ ከሚችለዉ አደጋ አንጻር (ለአምባገነኖቹ አገዛዝ የማያመቹ በመሆናቸዉ ካልሆነ) እንጂ በዘሩ ነዉ ብለን አናምንም” (ገጽ 8) ሲል፣- የአባባሉ ቀጥተኛ ትርጉም የሚሰጠን ህወሓት “አምባገነን” እንጂ “ጎሰኛ/ዘረኛ” አይደልም ማለት ነዉ፣፣ ይሄ በመጨረሻዉ ላይ ስለምመለስበት መጀመርያ ሌላዉ አስቀያሚ ወደ ሆነዉ “የታንድ” መግለጫ፣- ወያኔ በዘረፋም፣ በሽፋንም፣ በጋህድም በምኑም እያመካኘ የትግራይን ከተሞች እና ገጠሮች እያለማ ነዉ ለሚሉት ግለሰዎች/ድርጅቶች፣ በጸረ ትገሬነት መኮነኑን በሚመለከት ጉዳይ ትንሽ ልበል፣፣ በተለይም ታንድ ኢትዬጵያዊዉ ዶ/ር አሰፋ ነጋሽን በጸረ ትግሬነት ሲኮንን ዶ/ር አሰፋ ነጋሽ ጸረ-ትግሬ የሆነበትን ነጥብ አስካሁን ድረስ ማስቀመጥ አልቻለም። በደፋና “ስድብ መለጠፍ” “ስም ማጥፋት” ከታንድ የሚጠበቅ አይደለም እና ታንድም ሆኑ ሌሎቹ ዶ/ር አሰፋ ጸረ ትግራይ የሚያሰኘዉ አንዲት ነጥብ በማስረጃ በጽሁፍ አስደግፎ የቀረበልን አንድም ሰዉ ወይንም ድርጅት እስካሁን ማቅረብ አልተቻለም። ስለዚህ ስም መለጠፉ ይቁም ወይንም በማስጃ አስደግፎ ይቅረብ። ብዙ ሰዎች የሚያምኑትን፦ ማለትም አስካሁን ድረስ ወያነ ትግራይ በመንግሥትነት ተቀምጦ እየዘረፈና ሥልጣኑን ተጠቅሞ በተለያዩ መንገዶች የትግራይን ልማት ለማፋጠን የወሳዳቸዉ አድልኦዊ የበጀት እና የሰዉ አደረጃጀት ፍጥነት እና ጥራት እንዲሁም የፍጆታ አቅርቦትና ተጠቃሚነት ከተቀሩት ክፍላተ ሃገሮች ከሚኖሩ ነገዶች (ብዛት ያለዉም ይሁን ትንሽ ቁጥር ያለዉ)ዕድገት፣አደረጃጀት፣አቅርቦት እና ፍጆታ አድሎአዊ በሆነ መንገድ እያስተዳደረ መሆኑን ጸሃይ የሞቀዉ እዉነታ ነዉ። የዕድገታቸዉ ልዩነትም በዓይን የሚታይ መሆኑን እየታወቀ፣ ከሌሎቹ ጋር አወዳድሮ ማመሳከር የሚቻለዉን ወያኔ የወሰዳቸዉ ኢፍትሓዊ አርምጃዎችን በማስረጃ አስደግፎ መከራረከር ሲቻል በደፈናዉ አድሎአዊነት የተመረኮዘ የባጀት እና የሰዉ ሃይል ድልድል (አሎከሺን) አድሎአዊ የሆነ የሥራ አቀጣጠር፣ አድሎአዊ የሆነ የንግድ ፈቃድ አሰጣጥ እና “ፋስሊተሽን/እንክብካቤ”ተደርጓል ባልን ቁጥር “ጸረ- ትግራይ ህዝብ ናቸዉ” እያለ የሚኮንነን በአረጋዊ በርሀ እና በግደይ ዘርአጽየን የሚመራዉ “ታንድ” እራሱን የትግራይ ሕዝብ ተጠሪ እና አፈቀላጤ፣ተቆርቋሪ አድርጎ “ሲሾም” ፣ ከታንድ አመለካከት ዉጭ ያለነዉ የትግራይ ተወላጆች “ሕጋዊ የትግራይ” ልጆች አይደላችሁም ለማለት የሚዳዳዉ በሽታዉ ድሮ በራሃ እያሉ የትግራይ ተወላጆች የሆኑትን “የኢሕአፓ”መሪዎች እና ታጋዬች “ሕጋዊ የትግራይ ተጠሪዎች እና ትግሬዎች አይደላችሁም” በማለት ጎሰኛ ፖለቲካ ሲያራምዱት የነበረዉን በሽታቸዉ ከብዙ ዓመት በሗላ ያገረሻቸዉ ይመስላል፣፣ የታንድ መሪዎች ያልተረዱት ነገር፣- - - “ኢትዬጵያ አንድ ሕብረተሰብ እና ቤተሰብ ነዉ፣፣ ስለሆነም፣ እንኳን እና ከጎሳ ጎሳ የተደረገ አድልዎ ይቅር፣ ትግራይ ዉስጥ በትግራይ መሃል ዉስጥም ከቤተሰብ ወደ ቤተሰብ፣ በድረጅት አባልነት እና በድርጅት አባልነት በመንግሥት ባለሥልጣን ቅርበት እና ርቀት ሁሉ ጎሳዊ/ቤተሰባዊ አደልዎ ይደረጋል፣፣ የጎሰኛ ሥርዓት አስተዳደር የመጀመርያ ባሕሪ መመርያዉ አድሎአዊ አሰራር ማድረግ ነዉና ዜጎች አድልኦ ተደረገ ባሉ ቁጥር “ጸረ-… “ ጸረ-…” የሚል ቅጽል ስም መስጠት አንድም የጎሰኛ ባሕሪ አለመረዳት ነዉ ወይንም ሆን ተብሎ አደሎአዊ አስተዳደሩ እንዲቀጥል የሚደረግ ጥረት ነዉ፣፣ይሄ የእገሌ ጎሳ “መሳያ” (መድህን) እኛ ብቻ ነን የሚለዉ የወያኔ ነበር በሽታ ዛሬም ታንድ ኩፉኛ ሲጠናወተዉ ይታያል፣፣ ወያኔ ከሸዋ ከጎጃም ከጎንደር ከኦሮሞ….ሕዝብ ይልቅ ለትግራይ እና ለኤርትራ ጥብቅና እንደሚቆም “ታንድ”ራሱን ማሞኘት መብቱ ነዉ፣፣

Subscribe to:
Posts (Atom)